Bureau’s News

የዘላቂ ልማት ግቦች የ2017 የፈቃደኝነት ብሔራዊ ግምገማ ተካሄደ

የክልሉ የ2ኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የ2008 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግብ ከታቀደው ያነሰ ቢሆንም ቀጣይ ዕድገት ተመዝግቦበታል ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ከክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የዘላቂ ልማት ግቦች የ2017 የፈቃደኝነት ብሔራዊ ግምገማ እና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የ2008 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መዲና በሀዋሳ ተካሂዷል፡፡ 17 ዋና ዋና ግቦችና 169 ዝርዝር ግቦችን ይዞ የተነደፈው የዘላቂ ልማት ግቦች እ.ኤ.አ የ2016 ዓመት አፈጻጸም እንዲገመገም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሃሣብ ሲቀርብ ኢትዮጵያ ለማስገምገም ፈቀደኛ በመሆኗ ይኸው Read More …

የሴክተሩ አመራሮች ለልማት የሚመደበውን በጀት በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አስታወቁ

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሁሉም ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎችና ወረዳዎች የፋይናንስ ሴክተር ከፍተኛ አመራሮችን ያሳተፈ የንቅናቄ መድረክ ከጥር 17-18/2009 ዓ.ም በተካሄደበት ወቅት ለልማት የሚመደበውን በጀት በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል በየተሰማሩበት መስክ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አስታወቁ።የክልሉ የመስተንግዶ በጀት አመዳደብና አጠቃቀም ሁኔታ ሥርዓት ባለው መልኩና ወጥነት ባለው አሠራር ተግባራዊ እንዲደረግ፣ ለማስቻልና የበጀት ብክነትን በመቆጣጠር፣ የክልሉ የሀብት አጠቃቀም ይበልጥ በውጤታማነት እንዲተገበር ለማድረግ ታስቦ በተዘጋጀው መድረክ በመገኘት ንግግር ያደረጉት፣ የክልሉ ፋይናንሰና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ሲናገሩ፣ በየደረጃው በሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች ሊኖር የሚገባው Read More …

ሴቶች የተሟላ ነፃነትን ለመቀዳጀት ቁጠባን ባህል አድርገው ከኢኮኖሚ ጥገኝነት መላቀቅ እንዳለባቸው ተገለጸ

ይህ የተገለጸው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሠራተኞችና ማኔጅመንት አባላት ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ41ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ባከበሩበት ወቅት ነው፡፡“የሴቶችን የቁጠባ ባህል ማሳደግ ለህዳሴያችን መሠረት ነው” በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል ላይ ተገኝተው    የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ዓለማየሁ አይበራ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ባስተላለፉት መልዕክት በሕገ መንግሥታችን ለሴቶች እኩልነት ዕውቅና  ሲሰጥ ከሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች በመነሳት ሲሆን ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ፤ ልማትን አፋጥናለሁ የሚል መንግሥት ወይም ድርጅት የህብረተሰቡን 51 በመቶ የሚሆኑትን ሴቶች መብት ካላረጋገጠና ካለሳተፈ ሠላምና ዴሞክራሲ Read More …

በውጭ መንግሥታት የበጀት ድጋፍ ለሚካሄዱ ፕሮግራሞች ተገቢው ትኩረት መሰጠት እንዳለበት የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አስታወቀ

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ይህንን ያስታወቀው በውጭ መንግሥታትና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች የበጀት ድጋፍ በክልሉ የሚካሄዱ የቻናል አንድ ፕሮግራሞችን አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ቢሮው በተጨማሪ እንዳስታወቀው በተለያዩ የውጭ መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ በክልሉ የሚካሄዱ ፕሮግራሞች አፈጻጸም ደካማ በመሆኑ በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር በጀት ሥራ ላይ ሳይውል ለረጂ ድርጅቶች የሚመለስበት ሁኔታ እንዳለ ገልጿል፡፡ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ለሠራተኞችና ሥራ አመራር አባላት በተለይ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ተገኝተው ባሰሙት የመክፈቻ Read More …

የውጤት ተኮር ዕቅድ ተግባራዊነት የአፈጻጸም አመራር ሥርዓት የመፈጸም ብቃትን ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

የለውጥ መሣሪያ የሆነውን የውጤት ተኮር ዕቅድ በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግና የተወጠኑ ዕቅዶችን ወደ ውጤት መለወጥ፣ የአፈጻጸም አመራር ሥርዓትን  የመፈጸም ብቃት ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ ። በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የልማት ዕቅድ ዝግጅትና ኢኮኖሚ አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት፣ ለዞኖችና ልዩ ወረዳ ልማት ዕቅድ አስተባባሪዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፈው አማካሪ አቶ አለማየሁ አይበራ እንዳብራሩት፣ ሴክተሩ በተሀድሶ ወቅት የተለዩ ችግሮችን ትኩረት አድርጎ ወደ ንቅናቄ የገባ እንደመሆኑ ውጤታማነትን ለማስመዝገብ ከዕቅድ ዝግጀት እስከ ትግበራና ምዘና ድረስ ያለውን ሂደት እያንዳንዱ Read More …

የቢሮው ሠራተኞች በጥልቀት ተሀድሶው ሂደት የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትንና ተግባርን ለመናድ ቆርጠው መነሳታቸውን ገለጹ

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሠራተኞች በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ ላይ የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባር በመናድ በህዝብ አገልጋይነት ስሜት ብቁና ውጤታማ አገልግሎት ለማስመዝገብ ቆርጠው መነሳታቸውን ገለጹ። ከጥር 23-29/2009 ዓ.ም በቢሮው ሚሊኒዬም አዳራሽ “ብቁና ውጤታማ ፐብሊክ ሰርቪስ ለሀገራዊ ህዳሴ” በሚል ርዕስ በተካሄደው የመላው ሠራተኞችና ማናጅሜንት አባላት ግምገማ ወቅት እንደተገለጸው ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በሀገራችን የተመዘገበው ለውጥ፣የሁሉንም ዜጋ መብትና ተጠቃሚነትን ወደሚያረጋግጥበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እየገሠገሠ ቢሆንም በፐብሊክ ሰርቪሱ ዘንድ ልዩ ልዩ የአመለካከትና የተግባር ችግሮች መታየታቸው ተጠቅሷል ፡፡ በግምገማው ወቅት ከተጠቀሱት በፐብሊክ ሰርቪሱ ከሚታዩ Read More …

ቢሮው ለልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች የኤሌከትሮኒክስ ክፍያ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ዜጎችን የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ ለማድረግ በሚሠራው የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተሳታፊ ለሆኑ ተጠቃሚዎች፣ የሚሠጠውን ወርሃዊ ክፍያ ከመጪው ጥር 2009 ጀምሮ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አማካይነት አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ።ይህንን ያስታወቁት አቶ ተስፋዬ ታፈሠ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመንግስት ፋይናንሰ የሥራ ሂደት ባለቤት ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ሲሆን፣በክልሉ ሦስት ወረዳዎች ሙከራ ሲካሄድበት የቆየው ይህ የአከፋፈል ሥርዓት ጠቃሚነቱና ችግር አስወጋጅነቱ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ በቀጣይ ሸፋኑን በማስፋት በአሥራሁለት የክልሉ ወረዳዎች ተግባራዊ ለማድረግ ቅደመሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን ጠቅሰው ቀልጣፋና ወቅታዊ አገልግሎት ለመስጠትና ተጠቃሚዎችን ከእንግልት ለማዳን Read More …

የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሠራተኞች በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በማስቆም ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገቡ

በደቡብ፣ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሠራተኞች ይህንን ቃል የገቡት ዘንድሮ ለ11ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ያለውን የነጭ ሪቫንና የሕፃናት ቀን በዓልን በቢሮው ባከበሩበት ወቅት ነው፡፡ በቢሮው የልማት ዕቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ባለቤትና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ጡቄላ በዓሉን አስመልክቶ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር የኅብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶችን ከጥቃት በመከላከል ልማትን ማፋጠን ይቻላል ካሉ በኋላ የልማቱ አምራች የሆነው የሰው ሀብት ከጥቃት በመከላከልና ነፃና ዴሞክራሲያዊ መደላደሎችን በመፍጠር ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት Read More …

በቢሮው ዘጠነኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ

የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ማናጅሜንትና ሠራተኞች በሀገራችን ለዘጠነኛ ጊዜ የሚከበረውን ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ፣ በብዝሃነት ላይ ለተመሠረተው አንድነታችን አርማ ነው” በሚል መሪ ቃል በሴከተሩ  ቅጥር ግቢ በድምቀት ተከበሯል፡፡ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ታዳሚ ለሆኑ የማናጅሜንት አባላትና ሠራተኞች ወ/ሮ ምትኬ ገብረየስ  የኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ደጋፊ የሥራ ሂደት ባለቤት እንደተናገሩት፣ሰንደቅ ዓላማችን የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ የኃይማኖቶችና እምነቶች እኩልነት የሚገለጽበትና ህዝቦች ለሰንደቅ ዓላማ ያላቸውን ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የሚረዳ ሁነት መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር የህገ-መንግስታችን መሠረታዊ ሃሳቦችን ለማስረጽና ለማስተማር መልካም Read More …

24ኛው ዙር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሴክተር የምክክር ጉባኤ ያወጣው ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ

በአሁኑ ወቅት በሴክተሩ በየአሰተዳደር እርከኑ ያልተመጣጠነ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ሂደት መኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም በሴክተሩ በሁሉም አስተዳደር እርከኖች በለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ወጥነትና ጥልቀት ያለውን ሠራዊት በመገንባት ተግባራትን ለመፈፀም ቃል እንገባለን፡፡ በክልላችን በየአስተዳደር እርከኑ በተለያየ መልክ የሚገለፁና በ2008 በጀት ዓመት የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በተያዘው በጀት ዓመት የህዝብ ክንፍን፣ አመራሩንና ፈፃሚ አካላትን በፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ዙሪያ በማሳተፍ ይበልጥ ትግሉን በማጎልበት ችግሮቹ እንዲቀረፉ በማድረግ የላቀ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥና ለዚህ ዓላማ ስኬትም ተግተን ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡ ዘመናዊ የፋይናንስ አስተዳደርና ቁጥጥር Read More …