“ልዑል ማተሚያ ድርጅት” የፌዴራል መንግሥት፣ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መሥሪያ ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ዕገዳ ተጣለበት

“ልዑል ማተሚያ ድርጅት” በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመሥሪያ ቤቱን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶችና የቢሮ አቅጣጫ ጠቋሚ በማይካ ለማሠራት ያወጣውን ጨረታ ተወዳድሮ ካሸነፈና እስከ መስከረም 30 ቀን 2010 አጠናቆ ለማስረክብ በገባው ውል መሠረት ሠርቶ ካለማቅረቡም በላይ አድራሻውን በመሰወር በስልክ ቢጠራም ቀርቦ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሆኖ አልተገኘም፡፡

ስለሆነም በክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጁንና የግዥ አፈጻጸም መመሪያውን የጣሰ ጥፋት መፈጸሙን አረጋግጧል፡፡ በዚህ መሠረት ማተሚያ ድርጅቱ ከታህሣሥ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የአንድ ዓመት ዕገዳ የተላለፈበት ሲሆን የፌዴራል መንግሥት፣ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መሥሪያ ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ላይ ድርጅቱን እንዳያሳትፉ በደብዳቤ ተገልጾላቸዋል፡፡