የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የካይዘን ሥራ አመራር ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

kaizen news

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የካይዘን ሥራ አመራር ሥርዓትን በተቋሙ ተግባራዊ ለማደረግ መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡ ቢሮው ይህንን የገለጸው ለቢሮው ሠራተኞችና ማኔጅመንት አካላት ስለ ካይዘን ሥራ አመራር ፍልስፍና ባዘጋጀው ዐውደ ጥናት ላይ ነው፡፡

በቢሮው የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ዓባይነህ አቹላ በዐውደ ጥናቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የካይዘን ዳይሬክተሩ አያይዘውም ሥልጠናውን የወሰዱ ሁሉም ሠራተኞችና አመራር አካላት በቢሮው የካይዘን አምባሳደር በመሆን በ“ይቻላል”! መንፈስ ሥርዓቱን ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም የቢሮው ማኔጅመንት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሠረት የካይዘን ልማት ቡድን ተቋቁሞ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆን ይኖርብናል በማለት አስገንዝበዋል፡፡

የካይዘን ሥራ አመራር ሥርዓት በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት ተግባራዊ በመሆን ላይ ያለ ሲሆን ጃፓን ዛሬ ለደረሰችበት የዕድገት ደረጃም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከቱ ይታወቃል፡፡ ካይዘን ከሌሎች የለውጥ ሥራ ማሣሪያዎች ጋር ተዋህዶ በምርትና በአገልግሎት ሂደት ውስጥ የሚከሰት ብክነትን በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ፣ የምርትና የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ፣ ወጪን በመቀነስና አቅርቦትን በማሻሻል ስኬትን የሚያስገኝ ፍልስፍና ነው፡፡kaizen news

ከዚህም በመነሳት የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በቅጥር ግቢውና በሥራ ክፍሎች ውስጥ ተከማቸተው የሚገኙ አላስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በማስወገድ፣ ለሥራ ብቁ የሆኑትን መሣሪያዎች ደግሞ በመጠገን፣ በማፅዳትና በማደራጀት እንዲሁም ምቹ የሥራ አካባቢን በመፈጠር፣ የሠራተኛውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማጠናከርና የሥራ ተነሳሽነትን በማሳደግ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ አሠራርን በመከተል የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡