Human Resource Management

የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት የሚያከናውናቸው ተግባራት

  1. የሥራ ደረጃ ምዘና ጥያቄ ማቅረብ፣
  2. ልዩ ልዩ አበሎችና ጥቅማ ጥቅሞች በማጥናት ለክልሉ ዋና የሥራ ሂደት ማቀረብ፣
  3. በሰው ሀብት ሥራ አመራር ደንቦች፣ መመሪያዎችና መስፈርቶች ላይ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ መዋቅራቸውንና ተጠሪ ተቋማትን አቅም ማጎልበት፣
  4. በሰው ሀብት ሥራ አመራር አሠራሮች በተለይም በሰው ሀብት ማሟላት ተግባራት አፈጻጸም ላይ በሴክተራቸው እስከታችኛው መዋቅር የኢንስፔክሽን ሥራ ማከናወን፣ የአሠራር ግድፈት ባለባቸው አሠራሮች ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድና ስህተቱን የፈጸመው አካል በዲስፕሊን መመሪያ እንዲሁም ሌላ አግባብ ባለው ሕግ ተጠያቂ እንዲሆን የማድረግ፣
  5. በመዋቅራቸው በየደረጃው የሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚፈጸሙ የማሟላት ተግባራት ላይ የሚወሰዱ የእርምት እርምጃዎችን በተመለከተ ከክልሉ ዋና የሥራ ሂደት ጋር በጋራ ተቀናጅቶ የመሥራት፣
  6. ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ተግባራት በተጨማሪ የክልሉ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት በየደረጃው በሚገኙ ደጋፊ የሥራ ሂደቶች የሚከናወኑ ተግባራትን ማለትም የማሟላት የዲስፕሊን ጉዳዮችን የማየት የሰው ሀብት ልማት ሥራዎችን የማስተባበር፣
  7. ከታችኛው መዋቅር የሚተላለፉ ማናቸውንም የሰው ሀብት ማሟላት ክንውን መረጃዎች ሕጋዊነት በማረጋገጥ ለክልሉ ፐብሊክ ሠርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የማሰተላለፍና በማዕከል እንዲደራጁና ለተለያዩ ስታቲስቲካል መረጃዎች ግብአትነት እንዲውል ይረዳ ዘንድ ለሴክተሩ የሰው ሀብት መረጃና ስታትስቲክስ አቅርቦት የሥራ ሂደት ኮፒ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለባቸው፡፡