Public Finance Management

ምንን/ what / ይሠራል ለምን / why/ ይሠራል
የበጀትና የጥሬ ገንዘብ ዝውውር መፈፀም፤ በበጀት ለተደገፉ የልማት ፕሮግራሞችና የመንግስት አገልግሎቶች የሚያስፈልግ የገንዘብ አቅርቦት በወቅቱ በማድረስ ለታለመለትና አግባብ ላለው ዓላማ እንዲውል በማስፈለጉ፤
የተጠቃለለ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት ሠነድ ማዘጋጀት በፍላጎታቸው መሠረት የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ለመፈፀምና ለማስተዳደር፤
ክፍያ መፈፀም ለመንግስት የልማት ፕሮግራም፤ፖሊስዎች ግብዓት የሞሆኑ አገልግሎቶችና ንብረቶችን ለማቅረብ፤
ገቢን አጠቃሎ መቀበል በበጀት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካትና የወጪ ሽፋንን ለማሳደት፤
ወራሃዊና ዓመታዊ የተጠቃለለ የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀትና ማሰራጨት ለግብር ከፋዩ፤ለልማት አጋሮች እና ለሕብረተሰቡ ተፈላጊውን የሀብት አጠቃቀም መረጃ በመስጠት የግልጸኝነትና የተጠያቂነት አሰራር ለማስፈን ስለሚያስችል፤
የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት የመንግስት ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲሁም የሂሳብ ሪፖርት አቀራረብ በዕውቀት እንዲመራ ለማድረግ፤
የተሰብሳቢና የዕዳ ሂሳቦች መለየትና ማስተዳደር መንግስት መሰብሰብ ያለበት ገንዘብ በወቅቱ እንዲሰበሰብና ዕዳ እንዲከፈል ለማድረግ፤
የፀደቀ በጀት በመቀበል በበጀት ተቋም በወጪ ርዕስ በበጀት ዓይነትና በፋይናንስ ምንጭ ለይቶ በማደራጀት ማስተዳደርና መቆጣጠር የበጀት አስተዳደር አጠቃቀም ውጤታማ በማድረግ ለታለመለት ዓላማ ለማዋል፤
የባንክ ገቢና ወጪ ሂሳቦችን በመመዝገብ ሂሳብን ማስታረቅ የባንክ ገቢና ወጪ ሂሳብ ሚዛን በመዝገብ ከተመዘገበው ሂሳብ ጋር መታረቁን ለማረጋገጥ፤
የክልል ተቋማት ሂሳብ ማስተዳደርና  ሪፖርት ማዘጋጀት ተቋማት ዕቅዳቸውን እንዲያሳኩ የገንዘብ ፍሰት መፈጸምና የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተው ተደራሽ ማድረግ፤
ሂሳብ ማስመርመርና የማስተካከያ ሥራዎችን ማከናወን የውስጥ ስርዓት ለማጠናከር፤
የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት የሚመራባቸውን የሕግ ማዕቀፎችንና የአሰራር ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤ ማሰራጨትና ግንዛቤ ማስጨበጥ የመንግስት ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም በስርዓትና በዕውቀት እንዲመራ ለማድረግ ነው፡፡

Available Department’s Document

s.noDocuments' NameFile TypeDownload/View
1የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት የተሻሻለው የመዋቅር ጥናትPDFTo access click here