“ጫላላ ጠቅላላ ሕንፃ ተቋራጭ” የክልሉ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚፈጽሙት ማንኛውም ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ታገደ

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ “ጫላላ ጠቅላላ ሕንፃ ተቋራጭ” የክልሉ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚፈጽሙት ማንኛውም ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ የታገደ መሆኑን አስታወቀ::

ኤጀንሲው ይህንን ያስታወቀው ለፌዴራል የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡ በደብዳቤው እንደተገለጸው ጫላላ ጠቅላላ ሕንፃ ተቋራጭ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው የአካባቢ ማስታወቂያ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸለት በኋላ ቀርቦ ሥራውን መሥራት ሲገባው ይህንን ለመፈጸም ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱና የክልሉ መንግሥት የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት ጥፋተኛ ሆነው በመገኘቱ፣ ከህዳር 11/2010 ጀምሮ በሚታሰብ ለአንድ ዓመት የክልሉ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚፈጽሟቸው ማናቸውም ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ታግዷል፡፡